- Sputnik አፍሪካ, 1920
The African Heights show
ወቅታዊ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች፣ አዳዲስ መረጃዎች እና በደቡባዊው ዓለም ሀገራት መካከል ጠንካራ ትስስር የሚፈጥሩ አበይት ክስተቶች የሚዳሰሱበት ፕሮግራም።

አእምሮአዊ ሉዓላዊነት፦ የአፍሪካ ዕውቀት በማን ቁጥጥር ስር ነው?

አእምሮአዊ ሉዓላዊነት፦ የአፍሪካ ዕውቀት በማን ቁጥጥር ስር ነው?
ሰብስክራይብ
"ራሴን እንደ ምሁር ሳይሆን በህብረተሰቡ ውስጥ እንደ ተማሪ አድርጌ ባስቀመጥኩባቸው ጊዜያት ሁሉ፣ በቋንቋዎቻችን ውስጥ ያለውን ጥልቅ የፍልስፍና ይዘት ይበልጥ ለመረዳት ችያለሁ።[…]ሰዎች ባሉበት ሁሉ አስተሳሰብ አለ፤ አስተሳሰብ ባለበት ሁሉ እውቀት አለ፤ እውቀት ባለበት ሁሉ ደግሞ ፍልስፍና አለ፡፡” ሲሉ ደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ፕ/ር ሻባላኒ ኖኩቱላ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት የዛሬው የአፍሪካን ሃይትስ መሠኗዳችን በክፍል አንድ አፍሪካ የዲፕሎማሲያዊ ግኑኝነቷን የተቀናጀ እና የጋራ በማድረግ የውጪ ጣልቃ ገብነትን እንዴት መመከት ይቻላል በሚለው ርዕሰ ጉዳይ ላይ የዓለም አቀፍ ቢዝነስ አማካሪ ከሆኑት ዙበሪ ሊጂያና የተወያየን ሲሆን፤ በክፍል ሁለት ደግሞ የደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ መምህርት ፕ/ር ሻባናኒ ኖኩቱላ ጋር አፍሪካ የፖለቲካ ነፃነት ብታገኝም፣ ብዙ የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች አሁንም የአፍሪካን ታሪክ፣ ቋንቋዎች እና የእውቀት ሥርዓቶች ወደ ጎን በሚገፉ የቅኝ ግዛት ዘመን መዋቅሮች ውስጥ እየሰሩ ስለሚገኙበት ምክንያት፣ እነዚህ ውርሶች እንዴት እንደቀጠሉ እና መቀየር ስለሚቻልባቸው መንገዶች እንወያያለን፡፡
ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

አዳዲስ ዜናዎች
0