- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል። አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ይህ ፕሮግራምም ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

የምስራቃዊው እጥፋት፦ ሩሲያ ቻይና እና መካከለኛው ምስራቅ

ምስራቃዊው እጥፋት፡ ራሽያ፣ ቻይና እና አዲሱ መካከለኛው ምስራቅ
ሰብስክራይብ
በዓለማችን የኢነርጂ ገበያ ምስቅልቅል ውስጥ፣ የምዕራባውያንን የፋይናንስ አውታሮች እና የዋጋ መዋዠቅ የሚቋቋሙ አማራጭ የክፍያ ሥርዓቶች ለመዘርጋት ቻይናና ራሽያ የብሪክስን ጥረት እየመሩ ይገኛሉ።

ቻይና፣ ራሽያና ብሪክስ... ሉዓላዊ አገራት በዓለም አቀፍ ፀጥታ፣ ልማትና ንግድ እኩል ድምፅ የሚኖራቸው ባለብዙ ዋልታ ዓለም ሊፈጥሩ ይችላሉ። በብሪክስ ጉባኤ የሚነሱትም እነዚህ ጉዳዮች ናቸው፤ አገራቱ የዓለምን ሕዝብ 50% እና ኢኮኖሚ ከ40% በላይ ይይዛሉ” ሲሉ

ቆስጠንጢኖስ በርሁተስፋ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ።

በዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅት ሩሲያና ቻይና የምዕራባውያንን የበላይነት በመገዳደር ለአሜሪካ ጣልቃ ገብነት አማራጭ ማቅረባቸውን እና የአዲስ ምዕራፍ መሠረት መሆናቸውን እንቃኛለን። በጉዳዩ ላይ ከቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ አማካሪ እና የአፍሪካ ሕብረት ፀረ-ሙስና ቦርድ ሊቀመንበር ቆስጠንጢኖስ በርሁተስፋ (ዶ/ር) ጋር አውርተናል።

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Deezer – Afripods – Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0