ዚምቧቤ ከኤል ኒኖ ወቅት በፊት የምግብ አቅርቦትን ለመጠበቅ የሚረዳ ስድስት ቁልፍ እቅዶችን ይፋ አደረገች - መገናኛ ብዙኃን
ዚምቧቤ ከኤል ኒኖ ወቅት በፊት የምግብ አቅርቦትን ለመጠበቅ የሚረዳ ስድስት ቁልፍ እቅዶችን ይፋ አደረገች - መገናኛ ብዙኃን
የግብርና ሚኒስቴር ቋሚ ጸሐፊ ኦበርት ጂሪን ጠቅሰው መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት፤ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያፀደቀው ዕቅድ አነስተኛ ዝናብ በሚጠበቅበት የ2026-2027 ምርት ዘመን አርሶ አደሮችን ለመደገፍ እና በቂ የእህል ክምችት መኖሩን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሁሉን አቀፍ ምላሽ ወደ ተግባር እንዲገባ መንገድ ከፍቷል።
ስትራቴጂው የሚከተሉትን ያካትታል፦
1⃣ ለተጋላጭ የኅብረተሰብ ክፍሎች እህል ለማረጋገጥ ስትራቴጂካዊ የእህል ክምችትን ማጠናከር፣
2⃣ ለተጠቃሚዎች እና ለኢንዱስትሪዎች በቂ የእህል አቅርቦት ማቅረብ፤ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም ከውጭ የሚገቡ እህሎችን ማመቻቸት፣
3⃣ አርሶ አደሮች እርጥበትን እንዲጠብቁ እና ምርታቸውን ከገበያ ፍላጎት ጋር እንዲያገናኙ በማበረታታት የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም ግብርናን ማፋጠን፣
4⃣ የውሃ እና የመኖ ሀብቶችን በመከታተል ከድርቅ እንስሳትን የመጠበቅ ሥራ፣
5⃣ በባንኮች፣ በብሔራዊ የግብርና ማሳደጊያ እቅድ እና በግል ተቋራጮች በኩል የተቀናጀ የፋይናንስ መዋቅር መዘርጋት፣
6⃣ በግሉ ዘርፍ በሚመሩ ኮሚቴዎች በኩል ማስተባበር፡፡
ይህ ቅድመ ምላሽ ቀደም ሲል ከተከሰቱ ድርቆች የተወሰዱ ትምህርቶች መሠረት ያደረገ ነው ሲሉ ኦበርት ጂሪ ተናግረዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X