ሰላም ግንባታ ከዜጎች ጤና እና ደህንነት ውጭ ሌላ ምንም አይደለም - የቡሩንዲ የሰላማዊ ግጭት አፈታት ባለሙያ
ሰላም ግንባታ ከዜጎች ጤና እና ደህንነት ውጭ ሌላ ምንም አይደለም - የቡሩንዲ የሰላማዊ ግጭት አፈታት ባለሙያ
በጥሬ ዕቃዎች ሀብት የተሞላችው አፍሪካ አሁን የ"ኃያላን ሀገራት" ኢላማ ሆናለች ሲሉ በሰላማዊ ግጭት አፈታት ዙሪያ የቡሩንዲ ባለሙያ የሆኑት ሬሚ ሃቪያሪማና ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በአኅጉሪቱ የሚካሄዱ ጦርነቶች 'የውክልና ጦርነቶች' መሆናቸውንም አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል።
ብዙውን ጊዜ ህዝቦች ትእዛዙ ከየት እንደሚመጣ ሳያውቁ፣ የተለየ ጥቅም ያላቸውን የሌሎች አካላትን አጀንዳ ለማስፈጸም እርስ በእርስ ይዋጋሉ ሲሉ አብራርተዋል።
መስከረም 11 የተከበረውን ዓለም አቀፍ የሰላም ቀን ምክንያት በማድረግ ባለሙያው ሰላም እንዴት ሊረጋገጥ እንደሚችል ሲያስረዱ፦
ሀገራት በተናጥል እስካሉ ድረስ ሰላም ሊረጋገጥ አይችልም፤
ውሳኔዎች በመጀመሪያ በብሔራዊ፣ በክልላዊ እና በአካባቢያዊ ደረጃዎች እንዲወሰኑ አፍሪካ አንድ መሆን አለባት፤ ካልሆነ ግን እድገቱ የተገደበ ሆኖ ይቀጥላል፤
ሁሉም ቀውስ በዋናነት ኢኮኖሚያዊ ነው፦ በኢኮኖሚ አስተዳደር ውስጥ መልካም አስተዳደር ከሌለ ጦርነቶች ይቀጥላሉ።
አፍሪካውያን በሌሎች ቦታዎች ከተደረጉ ግኝቶች ጋር በመደገፍ 'አሁን እያለፉበት ካለው መከራ' ትምህርት ይወስዳሉ ብለዋል። ሁሉም ጥናቶች አፍሪካ የዓለም አቀፉ የወደፊት ተስፋ መሆኗን የሚያሳዩ በመሆናቸው፣ አፍሪካውያን በስተመጨረሻ አውሮፓን፣ አሜሪካን እና እስያን አልፈው ይጓዛሉ ሲሉ ሃቪያሪማና ጠቁመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X