- Sputnik አፍሪካ, 1920
Turning Africa Forward
በአህጉሪቱ ስልታዊ መነቃቃት ላይ ግልጽ እይታን የሚሰጥ በስፑትኒክ አፍሪካ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም ። ከዜናዎች ባሻገር፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላትን እየተለወጠ የመጣ ሚና በጥልቀት ይተነትናል፤ የወደፊቱን የዓለም ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ያለውን አቅጣጫ በሰፊው ይዳስሳል።

የአፍሪካ የስፖርት ባለቤትነት፣ የመሠረተ ልማት ግንባታ እና ሉአላዊነት ለአህጉራዊ ትስስር

የአፍሪካ የስፖርት ባለቤትነት፣ የመሠረተ ልማት ግንባታ እና ሉአላዊነት ለአህጉራዊ ትስስር
ሰብስክራይብ

ለአስርታት ዓመታት የአፍሪካ ወጣት አትሌቶች ውጤታማ ለመሆን፣ ዘመናዊ የስፖርት ሕክምና ለማግኘትና ተገቢውን ክፍያ ለማግኘት ወደ አውሮፓ ወይም አሜሪካ መሰደድ አለባቸው የሚል አስተሳሰብ ተጭኖብናል። ይህንን የምዝበራ ሥርዓት በመቀየር አፍሪካ የራሷን አትሌቶች፣ የስፖርት ሳይንስና የንግድ እሴት በሀገር ውስጥ የምታስቀርበትን 'የአትሌቲክስ ሉአላዊነት' ማረጋገጥ አለብን፤'' ሲሉ

የ'አፍሪካን ስፖርቲንግ ሴንቸሪ' (TASC) መሥራች ታሺንጋ ቺጌዴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በዛሬው ተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፕሮግራማችን፤ የአፍሪካን ስፖርት ክፍለ ዘመን እውን የማድረግ ስትራቴጂ፣ የስፖርት መሠረተ ልማቶችን በግልና በመንግሥት አጋርነት መገንባት፣ የነፃ ንግድ ቀጠናውን (AfCFTA) በመጠቀም የአህጉሪቱን የስፖርት ስርጭት መብት ማሳደግ፣ የስፖርት ሳይንስና የጾታ እኩልነትን ማረጋገጥ እንዲሁም አትሌቶቻችን በሀገራቸው ተገቢውን የኢኮኖሚ ጥቅም የሚያገኙበትን አሠራር በመዘርጋት ላይ ከታሺንጋ ቺጌዴ ጋር በጥልቀት ተወያይተናል።

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0