ኢትዮጵያ ዝቅተኛ የካርቦን ልቀት ያለውን የሲሚንቶ ምርት ለማስፋፋት ዓለም አቀፉን ጥረት ተቀላቀለች
19:10 23.09.2026 (የተሻሻለ: 19:14 23.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ዝቅተኛ የካርቦን ልቀት ያለውን የሲሚንቶ ምርት ለማስፋፋት ዓለም አቀፉን ጥረት ተቀላቀለች
እ.ኤ.አ በ2027 የሚካሄደውን የኮፖ32 የአየር ንብረት ጉባኤ ለማስተናገድ በዝግጅት ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ፣ የካርቦን ልቀትን የሚቀንሱ የተቀየጡ የሲሚንቶ ምርቶችን የሚያስፋፋውን “የተሻለ ውህድ ሲሚንቶ” ዓለም አቀፍ ንቅናቄ በይፋ ተቀላቅላለች።
የአዲሱ ትብብር አባላት እና ዓላማ፦
🟠 ኢትዮጵያ፣ ካምቦዲያ፣ ጋና፣ ታንዛኒያ እና ኡጋንዳ ትብብሩን በመቀላቀል የአባል ሀገራቱን ቁጥር ወደ 12 አሳድገዋል፡፡
🟠 ብራዚል፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ ኬንያ፣ ሉክሰምበርግ እና ኒውዚላንድ ቀደም ሲል ተቀላቅለዋል፡፡
🟠 ሀገራቱ የልማት ፕሮጀክት ግዢዎች ላይ የተቀየጠ ሲሚንቶን ቅድሚያ በመስጠት የግንባታ መስፈርቶችን ያሻሽላሉ።
የተቀየጠ ሲሚንቶ ለምን?
▪የልቀት ቅነሳ፦ በካርቦን የበለፀገውን ክሊንከር በሀገር ውስጥ ጥሬ ዕቃዎች በመተካት የካርቦን ልቀትን እስከ 50% ይቀንሳል።
▪አስተማማኝ ጥንካሬ፦ የግንባታ ጥንካሬን፣ ዘላቂነትን እና ወጪ ቆጣቢነትን ሳይቀንስ የአካባቢ ብክለትን ይከላከላል።
▪ዓለም አቀፍ ስጋት፦ ኮንክሪት ከዓለም አቀፍ የካርቦን ልቀት እስከ 8% የሚሸፍን በመሆኑ፣ አዳዲስ አረንጓዴ አማራጮችን መጠቀም ወሳኝ ሆኗል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X