ከ450 ሺህ በላይ አባወራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ 10 የመስኖ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ተድርገዋል - የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር

© telegram sputnik_ethiopiaከ450 ሺህ በላይ አባወራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ 10 የመስኖ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ተድርገዋል - የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር
ከ450 ሺህ በላይ አባወራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ 10 የመስኖ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ተድርገዋል - የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.09.2026
ሰብስክራይብ

ከ450 ሺህ በላይ አባወራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ 10 የመስኖ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ተድርገዋል - የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር

በመስኖ መሠረተ ልማት ግንባታ ዘርፍ ባለፉት ሁለት ዓመታት ዋና ዋና ግንባታቸው ተጠናቀው ወደ አገልግሎት የገቡና በማጠናቀቂያ ላይ የሚገኙ 10 የመስኖ ፕሮጀክቶች በአጠቃላይ 224 ሺህ 805 ሄክታር መሬት የማልማት አቅም እንዳላቸውም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

የፕሮጀክቶቹ የማልማት አቅምና የተጠቃሚዎች ቁጥር፦

የተንዳሆ መስኖ ፕሮጀክት፦ 60,000 ሄክታር የሚያልማ - 120,000

የከሰም መስኖ ፕሮጀክት፦ 20,000 ሄክታር - 40,000

ጊዳቦ (ሎት 2)፦ 13,420 ሄክታር - 26,840

ወልመል (ሎት 1 እና 2)፦ 12,040 ሄክታር - 24,080

ጎዴ መስኖ፦ 10,000 ሄክታር- 20,000

የቄጦ መስኖ፦ 5,000 ሄክታር - 10,000

ጨልጨል (ሎት 2)፦ 4,145 ሄክታር - 8,290

የታችኛው ርብ፦ 3,200 ሄክታር - 6,400 አባወራዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል

በተጨማሪም መሠረታዊ የግንባታ ሥራቸው ተጠናቆ የማጠናቀቂያ ሥራቸው እየተፋጠነ የሚገኙት የአርጆ ዲዴሳ እና የመገጭ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች በቅርቡ በይፋ ተመርቀው ወደ ሙሉ አገልግሎት የሚገቡ ይሆናል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0