ሩሲያ እና ኢትዮጵያ ለሕዝቦቻቸው የተሻለ መጪ ጊዜ በጋራ ለመሥራት በጥሩ ደረጃ ላይ ይገኛሉ - የሩሲያ የባሕል ማዕከል ዳይሬክተር

ሰብስክራይብ

ሩሲያ እና ኢትዮጵያ ለሕዝቦቻቸው የተሻለ መጪ ጊዜ በጋራ ለመሥራት በጥሩ ደረጃ ላይ ይገኛሉ - የሩሲያ የባሕል ማዕከል ዳይሬክተር

ሩሲያ እና ኢትዮጵያ ረጅም ዘመናት ያስቆጠረ ዲፕሎማሲያዊ፣ ሃይማኖታዊና ባሕላዊ ግንኙነት እንዳላቸው ዳይሬክተሩ ቭላዲሚር ጎሎቫቼቭ፤ የሞስኮ እና የመላው ሩሲያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ኪሪል 80ኛ ዓመት ልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀውን የፎቶግራፍ ዐውደ–ርዕይ በከፈቱበት ወቅት ገልጸዋል፡፡

 

የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጋር ያላትን ቁርኝት ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑንም ተናግረዋል።

"የሩሲያ የመንፈሳዊ ባሕል ቀናት" በኢትዮጵያ፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዓለ የሥነ ጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት ተከፍቷል። በተጨማሪም የሞስኮ እና የመላው ሩሲያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ኪሪል 80ኛ ዓመት ልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው "ለመላው ዓለም ሰላም" የተሰኘ የፎቶ ዐውደ–ርዕይ ለዕይታ ክፍት ተደርጓል፡፡

ስለሁነቱ የበለጠ ለማወቅ የስፑትኒክ አፍሪካን ቪዲዮ ይመልከቱ፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0