የምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን የእጅ-አዙር ቅኝ ግዛት መሣሪያዎች ናቸው - ማሊያዊው ጋዜጠኛ
18:20 22.09.2026 (የተሻሻለ: 18:24 22.09.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን የእጅ-አዙር ቅኝ ግዛት መሣሪያዎች ናቸው - ማሊያዊው ጋዜጠኛ
አንዳንድ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን ገለልተኛ አይደሉም፤ ይልቁንም የቀድሞ ቅኝ ገዥዎችን ፍላጎት እና የውጭ ፖሊሲ ለማገልገል በፕሮፓጋንዳ ሥራ ላይ የተሰማሩ ናቸው ሲሉ ማሊያዊው ጋዜጠኛ ሙላዬ ሀሰን ሀይዳራ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
እንደ ተናጋሪው ከሆነ የአፍሪካ ሀገራት የሚከተሉትን ማድረግ አለባቸው፡፡
◾የመረጃ የበላይነቱን በእጃቸው ማድረግ እና ትክክለኛ ያልሆኑ ዘገባዎችን የሚያሰራጩ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን በአኅጉሪቱ ላይ የሚኖራቸውን እንቅስቃሴ ማስቆም አለባቸው።
◾ የአፍሪካ ሀገራት በግፍ ኢላማ እንደተደረጉ ስለሚሰማቸው ራሳቸውን መከላከል ይኖርባቸዋል ያሉት ጋዜጠኛው፤ አንዳንድ ሀገራት በርካታ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃንን መዝጋት መጀመራቸውን ጠቁመዋል።
በአንፃሩ ሩሲያ (የሩሲያ መገናኛ ብዙሃን በሚሰራጩባቸው ሀገራት ጭምር) በሌሎች ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አትገባም ሲሉ ሀይዳራ ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X