ሩሲያ የትንሽ የጦር መሣሪያዎችን ክፍሎች በ3 ዲ ሕትመት ማምረት ጀመረች

ሰብስክራይብ

ሩሲያ የትንሽ የጦር መሣሪያዎችን ክፍሎች በ3 ዲ ሕትመት ማምረት ጀመረች

የሮስቴክ የአዲቲቭ ቴክኖሎጂዎች ማዕከል የምርት ጊዜን እና ወጪን የሚቀንሱ የጠመንጃ አፍ መቆጣጠሪያዎችን፣ ኮምፔንሴተሮችን እና የተኩስ ብልጭታ እሳት መደበቂያዎችን በ3ዲ ሕትመት ማምረት ጀምሯል።

ዋና ዋና ዝርዝሮች፦

🟠 በ3ዲ የታተሙት ክፍሎች ውስብስብ የውስጥ ጂኦሜትሪ ያላቸውና የተዋሃዱ ሲሆኑ፤ ቀደም ሲል በባህላዊ መንገድ ለማምረት ረጅም ጊዜ የሚወስዱ፣ ባለብዙ ደረጃ እና ለስህተት የተጋለጡ ነበሩ፡፡

🟠 ሀገር በቀል የቲታኒየም አሎይን እና ሌዘር የማቅለጥ ቴክኖሎጂን በመጠቀም፣ አጠቃላይ የሙከራ ምርቱ በከፍተኛ ፍጥነት በጥቂት የድህረ-ምርት ማስተካከያዎች በአንድ ቀን ውስጥ ተጠናቋል፡፡

🟠 እያንዳንዱ መሣሪያ ከ300 ግራም በታች የሚመዝን ሲሆን ከተለመዱት መሰል ምርቶች ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ ክብደት ያለው ነው። የተኩስ ንቅናቄን፣ የእሳት ፍንጣቂን እና ድምፅን ከመቀነሱም በላይ የተኳሹን ትክክለኛነት እና ምቾት ያሻሽላል።

ይህ ፕሮጀክት የምርት ፍጥነታችንን እና ለውስብስብ ክፍሎች የ3ዲ ሕትመት ያለውን ከፍተኛ አቅም ያሳየ ነው ሲሉ የማዕከሉ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አሌክሲ ማዛሎቭ ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0