ዚምባብዌ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሀገር አቀፍ የንግድ የድሮን ማጓጓዣ አገልግሎት ፈቃድ ሰጠች
19:25 21.09.2026 (የተሻሻለ: 19:34 21.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ዚምባብዌ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሀገር አቀፍ የንግድ የድሮን ማጓጓዣ አገልግሎት ፈቃድ ሰጠች
የዚምባብዌ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን "ድሮን ሶሉሽንስ ዚምባብዌ" ለተሰኘው ኩባንያ በሀገሪቱ የመጀመሪያውን ለሀገር አቀፍ የንግድ የድሮን ማጓጓዣ አገልግሎት ፈቃድ መስጠቱን ኩባንያው በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ አስታውቋል።
ድሮኖቹ ምን ያደርሳሉ?
ኩባንያው ይፋ እንዳደረገው፣ ልዩ ልዩ የመሸከም አቅም ያላቸው ድሮኖቹ የመድኃኒት አቅርቦቶችን፣ ክትባቶችን እና ፈጣን መልእክቶችን በማጓጓዝ በሀገሪቱ የነበረውን የመጨረሻው ማይል የሎጂስቲክስ ክፍተት ይደፍናሉ።
በቀርቡ እመርታ ላይ የተገነባ
ይህ ታሪካዊ ስኬት የተመዘገበው በቅርቡ በተሳካ ሁኔታ ከተካሄደው እና የተለመደውን የመሬት ላይ የጉዞ ጊዜ በግማሽ ከቀነሰው የ100 ኪሎ ሜትር በራሱ የሚንቀሳቀስ የድሮን በረራ ሙከራ በኋላ መሆኑን ኩባንያው አያይዞ አውስተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X