የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ በቻይና-አሜሪካ ግንኙነት እና በዓለም አቀፍ መረጋጋታ ላይ ለመምከር ወደ አሜሪካ ያመራሉ

© telegram sputnik_ethiopiaየቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ በቻይና-አሜሪካ ግንኙነት እና በዓለም አቀፍ መረጋጋታ ላይ ለመምከር ወደ አሜሪካ ያመራሉ
የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ በቻይና-አሜሪካ ግንኙነት እና በዓለም አቀፍ መረጋጋታ ላይ ለመምከር ወደ አሜሪካ ያመራሉ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 21.09.2026
ሰብስክራይብ

የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ በቻይና-አሜሪካ ግንኙነት እና በዓለም አቀፍ መረጋጋታ ላይ ለመምከር ወደ አሜሪካ ያመራሉ

የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተደረገላቸው ጥሪ መሠረት ከመስከረም 13 እስከ 15 ድረስ በአሜሪካ ይፋዊ ጉብኝት ያደርጋሉ።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እንዳስታወቁት፣ ሁለቱ መሪዎች በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፦

◼ በሁለትዮሽ ግንኙነቶች እና በቀጣይ አቅጣጫቸው ላይ ተፅዕኖ በሚፈጥሩ ቁልፍ ጉዳዮች፤

◼ በዓለም አቀፍ መረጋጋት እና በኢኮኖሚ ልማት ላይ ተፅዕኖ በሚያሳድሩ ዋና ዋና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች

የሀገር መሪዎቹ የሚያደርጉት ዲፕሎማሲ በቻይና እና አሜሪካ ግንኙነት ውስጥ የማይተካ ስትራቴጂካዊ ሚና እንደሚጫወት የጠቆሙት ቃል አቀባዩ፣ በስድስት ወራት ውስጥ በሺ እና በትራምፕ መካከል የሚደረጉት የርስ በርስ ጉብኝቶች ትልቅ ምዕራፍ መሆናቸውን ገልጸዋል።

አክለውም ቻይና ከአሜሪካ ጋር በመተባበር ግንኙነቱን ለማጠናከር፣ ውይይትና ትብብርን ለማጎልበት፣ ልዩነቶችን በአግባቡ ለመያዝ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ሰላምን፣ መረጋጋታንና ብልጸግናን ለማስፋፋት ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0