የደቡብ ሱዳን ከፍተኛ የኢሚግሬሽን ልዑክ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ስማርት ፖሊስ ጣቢያን ጎበኘ
17:05 21.09.2026 (የተሻሻለ: 17:14 21.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የደቡብ ሱዳን ከፍተኛ የኢሚግሬሽን ልዑክ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ስማርት ፖሊስ ጣቢያን ጎበኘ
በደቡብ ሱዳን የሲቪል ምዝገባ፣ ዜግነት፣ ፓስፖርትና ኢሚግሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሌተናንት ጀነራል አቾል ሲየር ሬሃን የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስን ዘመናዊ የስማርት ፖሊስ ጣቢያ አሠራርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ጎብኝቷል።
ልዑኩ በዲጂታል ቴክኖሎጂና በሰው ሠራሽ አስተውሎት የታገዘውንና ያለሰው ንክኪ ለሕብረተሰቡ ፈጣን አገልግሎት የሚሰጠውን የስማርት ፖሊስ ጣቢያ አሠራር ተመልክቷል።
የደቡብ ሱዳን ልዑካን በዲጂታል ሥርዓት የሚከናወነውን የዜጎች ጥቆማና አቤቱታ መቀበያ አሠራርና የወንጀል መከላከል ሥራዎችን በቦታው ተገኝተው ገምግመዋል።
የልዑካን ቡድኑ አባላት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያስመዘገበው ስኬት ለቀጣናው ሀገራት ትልቅ አርአያና የልምድ ልውውጥ መድረክ እንደሚሆን ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X