አል ሲሲ የሶማሊያን ሉዓላዊነት የሚጋፋ ጥሰት እንደማይቀበሉ ገለፁ

ሰብስክራይብ

አል ሲሲ የሶማሊያን ሉዓላዊነት የሚጋፋ ጥሰት እንደማይቀበሉ ገለፁ

​  አብደል ፋታህ ኤል-ሲሲ ከሲአይኤ ዳይሬክተር ጆን ራትክሊፍ ጋር ባደረጉት ውይይት ግብፅ ለሶማሊያ ደህንነት እና መረጋጋት ሙሉ ድጋፍ እንደምትሰጥ ማረጋገጣቸውን እና የሀገሪቱን ሉዓላዊነት፣ አንድነት ወይም ግዛት የሚጥስ ድርጊት አጥብቀው እንደሚቃወሙ መግለጻቸውን የፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

የግብፅ የስለላ ኃላፊ ሀሰን ራሻድን ባሳተፈው በዚህ ስብሰባ ውይይት የተደረገባቸው የሁለትዮሽ ስትራቴጂካዊ ግንኙነቶች እና ቀጣናዊ ጉዳዮች፦

​🟠 በኢራን ቀውስ ዙሪያ ሁሉን አቀፍ ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚደረጉ ጥረቶች፣

🟠 የጋዛን የተኩስ አቁም ማጠናከር፣

🟠 ለፍልስጤም ጉዳይ እልባት ለመስጠት የፖለቲካ ሂደቱን ዳግም ለመጀመር ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር፣

🟠 ለሱዳን ቀውስ እልባት መስጠት።

​የሲአይኤ ኃላፊ ግብፅ በመላው አፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ ለሰላም የምታበረክተውን አስተዋፅዖ አሜሪካ ታደንቃለች ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0