ኢትዮጵያ በሀገር አቀፍ ደረጃ የኤል ኒኖ ተጋላጭነትን በመለየት ምላሽ መስጠት የሚያስችል ዝግጁነት ላይ እንዳለች ገለፀች
20:40 20.09.2026 (የተሻሻለ: 20:44 20.09.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በሀገር አቀፍ ደረጃ የኤል ኒኖ ተጋላጭነትን በመለየት ምላሽ መስጠት የሚያስችል ዝግጁነት ላይ እንዳለች ገለፀች
የኤል ኒኖ ክስተት በምሥራቅ አፍሪካና በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች ከፍተኛ ድርቅ እና ጎርፍ ሊያስከትል እንደሚችል መረጃዎች ያመለክታሉ ሲሉ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አይድሩስ ሐሰን ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ገልጸዋል።
ተቋሙ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለኤል ኒኖ ክስተት ያለውን ተጋላጭነት መጠን የመለየት፣ የመቀነሻ እና የማቋቋሚያ ስትራቴጂ ማዘጋጀቱን አስታውቀዋል።
እስካሁን የተደረጉ ዝግጅቶች፦
ከፌዴራል እስከ ታችኛው መዋቅር ካሉ ሴክተሮች ጋር የቅድመ ዝግጅት ሥራ፣
በደቡብ ምሥራቅ እና ደቡብ ኢትዮጵያ ሊከሰት ከሚችለው የጎርፍ አደጋ ጋር ተያይዞ የምግብ፣ የምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች እና ቅጽበታዊ መሣሪያዎች ዝግጅት።
ምክትል ኮሚሽነሩ "በኢትዮጵያ ሰው ሠራሽም ይሁን የተፈጥሮ አደጋዎችን በራስ አቅም ለመቋቋም የሚያስችል ጠንካራ አቅም እየተገነባ ነው" ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X