ደቡብ አፍሪካ የአሜሪካን የስደተኞች ፖሊሲ "ሁለተኛው አፓርታይድ" ስትል ፈረጀች

ሰብስክራይብ

ደቡብ አፍሪካ የአሜሪካን የስደተኞች ፖሊሲ "ሁለተኛው አፓርታይድ" ስትል ፈረጀች

አሜሪካ በስደተኞች ፕሮግራሟ ለነጭ ደቡብ አፍሪካውያን (አፍሪካነርስ) ቅድሚያ ስትሰጥ፤ የደቡብ አፍሪካ ዲሞክራሲ ግን የትኛውም የማኅበረሰብ አባል "ያለ ምንም ገደብ አብሮ እንዲኖር" ይፈቅዳል ሲሉ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሮናልድ ላሞላ በዋሽንግተን በተካሄደው የአፍሪካ ዳያስፖራ ፎረም የፓናል ውይይት ወቅት ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ በዘር ላይ የተመሠረተው ይህ ፖሊሲ፤ በጥቁሮች ዕድገት እና በደቡብ አፍሪካ ኅብረ-ብሔራዊ ዲሞክራሲ ላይ የተሰነዘረ ጥቃት ነው ሲሉ ኮንነዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስተያየት አሜሪካ በአፍሪካነሮች ላይ ዘር ተኮር ወንጀል ይፈጸማል በማለት ደቡብ አፍሪካ ላይ የጣለችውን የቪዛ ገደብ የተመለከተ ነው። ፕሪቶሪያ ክሱ የሀገር ውስጥ ፖሊሲዎቿን የሳተ በማለት በጥብቅ ውድቅ አድርጋዋለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0