የሩሲያ ጥቃቶች ግዙፍ የዩክሬን የብረት አምራቾችን ከአገልግሎት ውጪ አደረጉ
19:12 20.09.2026 (የተሻሻለ: 20:14 20.09.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሩሲያ ጥቃቶች ግዙፍ የዩክሬን የብረት አምራቾችን ከአገልግሎት ውጪ አደረጉ
ሩሲያ በዛፖሮዥያ እና በዲኔፕሮፔትሮቭስክ ክልሎች የሚገኙ የሀገሪቱ ሦስት ትላልቅ የብረት ፋብሪካዎች መምታቷን ተከተሎ የዩክሬን የብረት ኢንዱስትሪ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ቆሟል ሲል ፋይናንሻል ታይምስ ቅርብ የኢንዱስትሪው ሰዎችን ጠቅሶ ዘግቧል።
ጉዳት ከደረሰባቸው ተቋማት ቀደም ሲል የዩክሬንን 90% የብረት ምርት ይሸፍኑ የነበሩት የሜትኢንቨስት ፋብሪካዎች እና በክሪቮይ ሮግ የሚገኘው የአርሴለርሚታል የብረት ፋብሪካ ተጠቃሽ ናቸው። ፋብሪካዎቹ ሥራ ማቆማቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞችን ከሥራ ውጪ ያደረገ ከመሆኑም በላይ በኢንዱስትሪ ምርት፣ በታክስ ገቢ እና በአጠቃላይ ኢኮኖሚው ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል።
“ከዛሬ ጀምሮ [ዩክሬን] የብረት ኢንዱስትሪ የላትም" ሲሉ የሜትኢንቨስት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቢሮ ኃላፊ ኦሌክሳንደር ቮዶቪዝ ተናግረዋል።
ይህ መስተጓጎል ቁልፍ የዩክሬን የኢንዱስትሪ መሠረተ ልማቶቾ በሩሲያ ጥቃቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ ተፅዕኖ ሥር መውደቃቸውን ያመላክታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X