ለኢራን የ 'ጦርነት ወይም ድርድር' አማራጭ ተቀባይነት የለውም - የኢራን ፓርላማ አፈ-ጉባኤ
17:20 20.09.2026 (የተሻሻለ: 17:24 20.09.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ለኢራን የ 'ጦርነት ወይም ድርድር' አማራጭ ተቀባይነት የለውም - የኢራን ፓርላማ አፈ-ጉባኤ
"አንድ አካል እየተዋጋ መደራደርም ስለሚኖርበት 'የጦርነት ወይም ድርድር' አማራጭ የተሳሳተ ነው ብለን እናምናለን" ሲሉ መሐመድ- ባገር ጋሊባፍ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።
አፈ-ጉባኤው በመግለጫቸው ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦
ኢራን ጠንካራ አቋም በመያዝ በጥበብ መዋጋት እና በትክክለኛው ጊዜ መደራደር አለባት፣
ይህ ጊዜው ሲመች ባለን ወታደራዊ አቅም ሁሉ ጠላትን መመከት እና አንበርካኪ ምት ማሳረፍ ማለት ነው፣
በውጊያው ጉልህ ድል ካስመዘገብን እና ጠላትን ካዳከምን በኋላ ያገኘነውን ስኬት ለማጠናከር፣ አቋማችንን ለማጎልበት እና አለመደፈራችንን ለማረጋገጥ ዲፕሎማሲን መጠቀም አለብን፣
ወቅታዊ የዲፕሎማሲ አቋማችን ሙሉ በሙሉ ግልጽ፣ ምክንያታዊ እና ለድርድር የማይቀርብ ነው፣
ቅድመ ሁኔታዎቻችንን በአሸማጋዩቻችን በኩል በግልጽ ያሳወቅን ሲሆን ጠላትም ማታለል እና የአንድ ወገን ፍላጎት ከእንግዲህ ተቀባይነት እንደሌለው ተገንዝቧል፣
እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች እስካልተሟሉ፣ የኢራን ሕጋዊ መብቶች እስካልተከበሩ እና አሜሪካ ገብታ የነበረችውን ቃል እስካልፈጸመች ድረስ፤ ወደ ድርድር መመለስም ሆነ የሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ መከፈት አይታሰብም።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X