ኢትዮጵያ ሀገር በቀል ዕፅዋትን ከመጥፋት ለመታደግ እንቅስቃሴ ጀመረች
16:54 20.09.2026 (የተሻሻለ: 17:04 20.09.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ሀገር በቀል ዕፅዋትን ከመጥፋት ለመታደግ እንቅስቃሴ ጀመረች
ጥረቱ በአፋር እና ሶማሌ አካባቢዎች የሚገኙ በወራሪ ዕፅዋት፣ በትላልቅ ዛፎች በመሸፈን እንዲሁም በከፍተኛ የከብት ግጦሽ የመጥፋት አደጋ ውስጥ የገቡ ሀገር በቀል እጽዋት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው።
🫘 ዕፅዋቱን ለመታደግም ዝርያዎችን በዘረመል ባንክ የማስቀመጥ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል ሲል የኢትዮጵያ ብዝኃ-ህይወት ኢንስቲትዩት አስታውቋል።
ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የወደሙ አካባቢዎችን በሀገር በቀል ዖፅዋት ችግኞች ብቻ መልሶ የማልማት ሥራ እየተሠራ ነው መባሉን ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
በኢትዮጵያ ከ6 ሺህ 500 በላይ ሀገር በቀል የዕፅዋት ዝርያዎች ይገኛሉ።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X