በማሊ ዲዩራ የጦር ሠፈር ጥቃት የውጭ ሀገር ቅጥረኛ ተዋጊዎች ተሳትፈዋል - የሀገሪቱ ጦር መግለጫ

© telegram sputnik_ethiopiaበማሊ ዲዩራ የጦር ሠፈር ጥቃት የውጭ ሀገር ቅጥረኛ ተዋጊዎች ተሳትፈዋል - የሀገሪቱ ጦር መግለጫ
በማሊ ዲዩራ የጦር ሠፈር ጥቃት የውጭ ሀገር ቅጥረኛ ተዋጊዎች ተሳትፈዋል - የሀገሪቱ ጦር መግለጫ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 20.09.2026
ሰብስክራይብ

በማሊ ዲዩራ የጦር ሠፈር ጥቃት የውጭ ሀገር ቅጥረኛ ተዋጊዎች ተሳትፈዋል - የሀገሪቱ ጦር መግለጫ

ሽብርተኝነትን በሚደግፉ የተወሰኑ ሀገራት የታጠቁ የውጭ ሀገር ተዋጊዎች ከአዝዋድ የነጻነት ግንባር (ኤፍኤልኤ) እና ጃማት ኑስራት አል-ኢስላም ዋል-ሙስሊምን (ጅኒም*) አባላት ጋር በመሆን በጥቃቱ ላይ መሳተፋቸውን የማሊ ጦር ኃይል አስታውቋል።

የማሊ ጦር ተጨማሪ መግለጫዎች፦

የማሊ ወታደሮች ከጦር ሠፈሩ አቅራቢያ እና በዲዩራ ዳርቻዎች በሚገኙ ቀሪ የጠላት ምሽጎች ላይ ቅዳሜ የተነጣጣሩ ጥቃቶች ማካሄዳቸውን ቀጥለዋል።

የጦር ኃይሉ በሽብር ቡድኖች ላይ "ከባድ የሰው እና የንብረት ጉዳት" ማድረሱን አስታውቋል።

ወታደራዊ ኃይሉ ትክክለኛው ቁጥር ባይገልጽም፤ በወታደሮቹ ህይወት ማለፍ የተሰማውን ቁጭት ገልጻል።

ዘመቻው ከሳምንት በላይ የፈጀ ነበር።

በዲዩራ ወታደራዊ ሠፈር ላይ ስለተፈጸመው የሽብር ጥቃት ዝርዝር መረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣው ጷጉሜ 5 ቀን ነበር። ክስተቱን ተከትሎ የጦር ኃይሉ ቃል አቀባይ ባካሪ ቦካር ማይጋ በፈጣን የአየር እና የምድር ምላሽ የጠላት ኢላማዎች መደምሰሳቸውን አስታውቀዋል።

*ጅኒም የኤፍኤልኤ አጋር እና ከዓለም አቀፉ የሽብር ድርጅት አልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያለው አሸባሪ ነው

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0