ብሪክስ በአፍሪካ ልማት ውስጥ 'ወሳኝ' ሚና ሊጫወት ይችላል - የደቡብ አፍሪካዊ ሥራ ፈጣሪ
ብሪክስ በአፍሪካ ልማት ውስጥ 'ወሳኝ' ሚና ሊጫወት ይችላል - የደቡብ አፍሪካዊ ሥራ ፈጣሪ
በተለይም አማራጭ የንግድ ሞዴሎች ብቅ እያሉ በመሆናቸው ስብስቡ በአፍሪካ ልማት ውስጥ ቁልፍ ሚና ሊጫወት ይችላል ሲሉ የ 'ፍሬንድስ ኦፍ ብሪክስ+ ሶሳይቲ' ተባባሪ መስራች ካርሊንድ ጎቨንደር በሞስኮ ከተካሄደው ሁለተኛው የዓለም ሕዝባዊ ጉባኤ ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
የሥራ ፈጣሪው ዋና ዋና ሞልከታዎች፦
🟠 ስለ ብሪክስ እና አፍሪካ፦ ቻይና ለአፍሪካ ንግድ የዘረጋችውን ከቀረጥ ነፃ ሥርዓት፤ ቀረጥን "እንደ መሳሪያ" ከሚጠቀሙ ሌሎች ኃይሎች ጋር አነጻጽረው እንደ በጎ ጅማሮ ጠቅሰውታል። የሚገኙት ጥቅሞች ልሂቃንን ብቻ ሳይሆን፤ በዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ላይ ለሚገኙ ሥራ ፈጣሪዎች መድረሳቸውን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል።
🟠 ስለ ፋይናንስ ሥርዓት ማሻሻያ፦ አይ.ኤም.ኤፍ እና የዓለም ባንክ ለአፍሪካ ሀገራት የሚሰጡትን ከፍተኛ ብድር "የቅኝ አገዛዝ ኢምፔሪያሊዝም ፕሮጀክትን ለማስቀጠል የሚጠቀሙበት ስትራቴጂካዊ መንገድ" በማለት ተንታኙ ተችተዋል። "የፋይናንስ አካታችነት እና ኢኮኖሚያዊ ክብርን" ለማሳደግ የባንክ ዘርፉን ማሻሻል እንደሚያስፈልግ ጥሪ አቅርበው፤ "የባንክ አገልግሎት ሰብዓዊ መብት ነው" ብለዋል።
🟠 ስለ ሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ፦ የአፍሪካ መሪዎች በመጪው ጉባኤ "ለላቀ ትብብር እና ጥገኝነትን ለመቀነስ" ቅድሚያ መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል። ቀዳሚ የትኩረት አቅጣጫዎች ትምህርት፣ በገጠር አካባቢዎች የዲጂታል ቴክኖሎጂን ተደራሽ ማድረግ፣ ኢነርጂ እና ግብርና ናቸው ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X