የአፍሪካ ታዛቢዎች የሩሲያን በላቀ ቴክኖሎጂ የታገዘ ምርጫ አወደሱ

ሰብስክራይብ

የአፍሪካ ታዛቢዎች የሩሲያን በላቀ ቴክኖሎጂ የታገዘ ምርጫ አወደሱ

​ ከኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ማሊ የመጡ ታዛቢዎች የሩሲያ የምርጫ ሂደት ግልጽነት እና የላቀ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ለአፍሪካ ሀገራት ጥሩ መሳያ ሊሆን እንደሚችል በማጉላት አወድሰውታል። አስተያየታቸው ከዓርብ ጀምሮ ለሦስት ቀናት እየተካሄደ ያለውን የሩሲያ ስቴት ዱማ (ፓርላማ) ምርጫ የተመለከተ ነው።

የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች፦

​🟠 የዲ.አር. ኮንጎ ታዛቢ፦ ዲ.አር. ኮንጎን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ከሩሲያ የምርጫ ቴክኖሎጂዎች እና ልምድ ሊጠቀሙ ይችላሉ ሲሉ የዲ.አር. ኮንጎ ገለልተኛ ብሔራዊ ምርጫ ኮሚሽን አባል አዲን ኦሞኮኮ አሳሞቶ ለስፑትኒክ ተናግረዋል። የኤሌክትሮኒክስ የድምጽ መስጫ ማሽኖቹን "ፍጹም" በማለት ያደነቁ ሲሆን በሩሲያ መራጮች ዘንድ ያለውን ከፍተኛ የዲጂታል እውቀትና ክህሎትም አንስተዋል።

​🟠 የማሊ ታዛቢ፦ የሩሲያ ምርጫ ታማኝነት "ምንም ጥያቄ ውስጥ አይገባም" ሲሉ የማሊ ገለልተኛ የምርጫ አስተዳደር ባለሥልጣን ሪፖርተር ብራኪማ ፎምባ ለሩሲያ ሚዲያ ተናግረዋል። ለዚህም ማጭበርበርን የሚከላከለውን በኮምፒውተር የተደገፈ ስርዓት ጠቅሰዋል። ሥርዓቱን ግልጽ ምርጫ ማድረግ ለሚፈልጉ የአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ ሲሉ ገልጸውታል።

​እስከ እሁድ የሚዘልቀው የፓርላማ ምርጫ፤ የዶንባስ እና ኖቮሮሲያ ነዋሪዎች ሲሳተፉበት የመጀመሪያው ነው። መራጮች በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች የኤሌክትሮኒክስ ማሽኖችን መጠቀም ይችላሉ።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ቫለንቲና ማትቪየንኮ በፓርላማ ምርጫ ድምፃቸውን ሲሰጡ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0