ኢትዮጵያ የኒውክሌር ካንሰር ሕክምናን በማስፋፋት የጤና መሠረተ ልማቷን አጠናከረች
20:32 19.09.2026 (የተሻሻለ: 20:34 19.09.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የኒውክሌር ካንሰር ሕክምናን በማስፋፋት የጤና መሠረተ ልማቷን አጠናከረች
በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ የሕክምና ማዕከላት አገልግሎት መስጠት በመጀመራቸው ኢትዮጵያ የኒውክሌር እና የሬዲዮቴራፒ ተኮር የካንሰር ሕክምና ተዳራሽነቷን እያሰፋች እንደምትገኝ የኒውክሌር ኢነርጂ ኮሚሽን ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ገልጿል።
ቀደም ሲል የሀገሪቱ ብቸኛ የኒውክሌር ካንሰር ሕክምና ማዕከል በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ውስጥ የሚገኘው ብቻ ነበር።
አሁን በሐዋሳ፣ በጅማ፣ በሐረማያ፣ በጎንደር እና አዲስ አበባ በሚገኘው ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አምስት ተጨማሪ ማዕከላት ተከፍተዋል።
በመቀሌ የሚገኘው ሌላኛው ማዕከል ደግሞ ግንባታ ላይ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኢነርጂ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አብዱራዛቅ ኡመር ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X