የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በዓለም ከፍተኛ ትስስር ካላቸው 50 ማረፊያዎች አንዱ ሆነ
20:06 18.09.2026 (የተሻሻለ: 20:14 18.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በዓለም ከፍተኛ ትስስር ካላቸው 50 ማረፊያዎች አንዱ ሆነ
ዓለም አቀፉ የአቪዬሽን መረጃ አቅራቢ ድርጅት ባወጣው አዲሱ የ2026 ሪፖርት የተካተቱት የአፍሪካ አውሮፕላን ማረፊያዎች የኢትዮጵያው እና የደቡብ አፍሪካው (ኦአር ታምቦ) ብቻ ናቸው።
የሪፖርቱ ቁልፍ ዝርዝሮች፦
የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ (50ኛ ደረጃ)፦ ባለፈው ዓመት ከነበረበት 60ኛ ደረጃ 10 ደረጃዎችን በማሻሻል ከፍተኛ ዕድገት አሳይቷል።
94% የሚሆነው የአውሮፕላን ማረፊያው በረራ የሚካሄደው በኢትዮጵያ አየር መንገድ ብቻ ነው።
ኦአር ታምቦ፦ ደቡብ አፍሪካ (40ኛ ደረጃ)፦ ባለፈው ዓመት ከነበረበት 38ኛ ደረጃ ወደ 40ኛ ዝቅ ብሏል።
በማረፊያው 35% የሚሆነውን በረራ የሚሸፍነው "ኤርሊንክ" የተሰኘው የሀገሪቱ አየር መንገድ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X