ከኢል ኒኖ ጋር በተያያዘ አርሶ አደሩ የደረሱ አዘርቶችን በቶሎ እንዲሰበስብ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳሰበ
17:30 18.09.2026 (የተሻሻለ: 17:34 18.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ከኢል ኒኖ ጋር በተያያዘ አርሶ አደሩ የደረሱ አዘርቶችን በቶሎ እንዲሰበስብ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳሰበ
የመካከለኛው ፓስፊክ ውቅያኖስ እንዲሁም የምዕራብ ህንድ ውቅያኖስ ሙቀት ከጥቅምት አጋማሽ በኋላ ኢል ኒኖ ሊያስከስት እንደሚችል የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አሳምነው ተሾመ ተናግረዋል።
ይህም "ወቅቱን ያለጠበቀ ዝናብ እንዲኖር አስተዋጽኦ ያደርጋል” ብለዋል።
የአየር ሁኔታው የሚመለከታቸው የሀገሪቱ ክፍሎች የቶቹ ናቸው?
▪ ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ፣
▪ ሰሜን ምሥራቅ እና መካከለኛው ኢትዮጵያ፣
▪ ምሥራቅ ኢትዮጵያ።
ኢንስቲትዩቱ በሚሰጠው ትንበያ መሠረት ቅድመ ዝግጅትና የምላሽ እርምጃ መወሰድ እንዳለበትም አመልክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X