ኢትዮጵያ በቴምር ምርት ራስን ለመቻል የ10 ዓመት ዕቅድ ይፋ አደረገች
16:35 18.09.2026 (የተሻሻለ: 16:44 18.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በቴምር ምርት ራስን ለመቻል የ10 ዓመት ዕቅድ ይፋ አደረገች
የሀገሪቱ የቴምር ምርት ዝቅተኛ በመሆኑ ፍራፍሬውን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እየፈሰሰ ነው ሲል የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል።
የ10 ዓመት ዕቅዱ ምርት የማስፋት እና የቴምር ወጪ ንግድ አቅምን የማሳደግ ውጥን ያነገበ ነው።
▪ ኢትዮጵያ ከ500 ሺህ-700 ሺህ ሄክታር ለቴምር ልማት ተስማሚ የሆነ መሬት አላት፣
▪ ጥቅም ላይ የዋለው 6 ሺህ ሄክታር ብቻ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ጋር በመተባበር የሚካሄደው ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የቴምር ፌስቲቫል ከመስከረም 10-12 በሰመራ ከተማ ይካሄዳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X