300 የህወሓት ታጣቂዎች መሣሪያቸውን አስረክበው ለመከላከያ ሠራዊት እጃቸውን ሠጡ

ሰብስክራይብ

300 የህወሓት ታጣቂዎች መሣሪያቸውን አስረክበው ለመከላከያ ሠራዊት እጃቸውን ሠጡ

 

ተዋጊዎቹ ህወሃት ከኤርትራ ጋር የፈጠረው የፅምዶ ጥምረት ለትግራይ ሕዝብ የማይጠቅምና የሚጎዳ መሆኑን በመገንዘብ ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሰሜን ምዕራብ ዕዝ እጅ ሠጥተዋል።

 

ለዕዙ ገቢ የሆኑ መሣሪያዎች፦

280+ የነፍሰ ወከፍና የቡድን መሣሪያዎች፣

በርካታ የተለያዩ ዓይነት ተተኳሾች፣

የጦር ሜዳ መነፅርና ልዩ ልዩ ዶክመንቶች።

በተጨማሪም የህወሃት አገዛዝን በመጥላትና ሠላምን በመምረጥ እጅ ለመስጠት የሚጠባበቁ በርካታ የትግራይ ወጣቶች እንዳሉ ታጣቂዎቹ መግለጻቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0