የአፍሪካ ታዛቢዎች የሩሲያ የፓርላማ ምርጫ በጥሩ ሁኔታ መጀመሩን አደነቁ
14:05 18.09.2026 (የተሻሻለ: 14:14 18.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ታዛቢዎች የሩሲያ የፓርላማ ምርጫ በጥሩ ሁኔታ መጀመሩን አደነቁ
የኮሞሮስ፣ ቡሩንዲ እና ካሜሩን ታዛቢዎች በመጀመሪያው የድምፅ መስጫ ቀን በሞስኮ በሚገኝ የድምፅ መስጫ ጣቢያ መድረሳቸውን የስፑትኒክ ዘጋቢ ዘግቧል።
ታዛቢዎቹ በምርጫ ጣቢያው የሚከተሉትን ነጥቦች ገምግመዋል፦
◻ የሂደቱን አጠቃላይ አደረጃጀት፣
◻ በምርጫ ጣቢያዎች ያለውን የቴክኖሎጂ ዝግጅት ደረጃ፣
◻ የድምፅ መስጠት ሂደቱን ተዓማኒነት።
የኮሞሮስ ደሴቶች ተወካይ ሁሳም ኤዲን ዳዉድ፤ የምርጫ ጣቢያው በተከፈተ የመጀመሪያው አንድ ሰዓት ውስጥ እሳቸውም ሆኑ ባልደረቦቻቸው ምንም ዓይነት መታወክ፣ ጥሰት ወይም ችግር እንዳላዩ እና ድምፅ የመስጠት ሂደቱ በሰላም ያለ ምንም ችግር እየተካሄደ መሆኑን ለስፑትኒክ ገልጸዋል።
በተጨማሪም ከአልጄሪያ የመጡ ተወካይ በምርጫ ጣቢያዎች ከታዛቢዎቹ ጎን መገኘታቸውን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
የ9ኛው የስቴት ዱማ አባላት እና ሌሎች ተዛማጅ ምርጫዎች በዛሬው ዕለት ተጀምረዋል። ድምፅ አሰጣጥ እስከ እሑድ ይቀጥላል።
በዚህ ምርጫ በአጠቃላይ 20 ሺህ 700 የፌዴራል፣ ክልል እና የከተማ አስተዳደር ፓርላማ ወንበሮች እና የኃላፊነት ቦታዎች ይሞላሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia

© telegram sputnik_ethiopia