- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል። አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ይህ ፕሮግራምም ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

ከድንጋይ ወደ ሀብት፡ የአፍሪካ የእሴት አብዮት

ከድንጋይ ወደ ሀብት፡ የአፍሪካ የእሴት አብዮት
ሰብስክራይብ
አፍሪካ ጥሬ ማዕድናትን ወደ ውጭ መላክ ላይ ገደቦችን በመጣል ከሀብት ማውጣት ብቻ ባለፈ የእሴት ሰንሰለቶችን በመገንባት፣ ሥራዎችን በመፍጠር እና እሴትን በሀገር ውስጥ ለማስቀረት እየተሸጋገረች ይገኛል።

አፍሪካ ጥሬ እቃዎችን በመላክ ላይ ማተኮሯ ለኢኮኖሚ ልማት ጠቃሚ አይደለም፤ እንደ ሊቲየም እና ኮባልት ያሉ ስትራቴጂካዊ ማዕድናት ውጭ እንዳይወጡ መከልከልም ኩባንያዎች ምርቶቹን በሀገር ውስጥ እንዲያጸዱ ያስገድዳቸዋል" ሲሉ መሐመድ

ኢብራሂም ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

የዛሬው ድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅት የአፍሪካ ሀገራት ያልተቀነባበሩ ማዕድናትን ወደ ውጭ መላክ የመከልከል እንቅስቃሴዎችን ይቃኛል። በዚህም አፍሪካ ሀብቷን በሀገር ውስጥ በማስቀረት እሴት መፍጠር መጀመሯን እንመለከታለን። በጉዳዩ ላይ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ኢኮኖሚ ጉዳዮች ተመራማሪ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኝ መሐመድ ኢብራሂም ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezerAfripods SpotifyPocket CastsPodcast AddictCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0