በአራት ክልሎች የሚገኙ ታሪካዊና ባሕላዊ ቅርሶች ዕድሳታቸው ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሊደረጉ እንደሆነ ተገለፀ
20:28 17.09.2026 (የተሻሻለ: 20:34 17.09.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በአራት ክልሎች የሚገኙ ታሪካዊና ባሕላዊ ቅርሶች ዕድሳታቸው ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሊደረጉ እንደሆነ ተገለፀ
በኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን የቅርስ ጥበቃና ልማት መሪ ቅርሶቹ በያዝነው ወር ለሕዝብ ዕይታ ክፍት እንደሚሆኑ ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ገልጸዋል።
እንደ ኃላፊው ገለጻ ለአገልግሎት ዝግጁ የሆኑት ቅርሶች ከታች የተጠቀሱት ናቸው፦
በአማራ ክልል የሚገኘው የቅዱስ ማርቆስ ቤተ-ክርስቲያን የግድግዳ ሥዕል፣
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኘው የደጃዝማች መሐመድ ባንጃው ቤተ-መንግሥት፣
በትግራይ ክልል የሓ ከተማ የሚገኘው የአቡነ ሃፊፄ ቤተ-ክርስቲያን፣
በአፋር ክልል የሚገኘው የሱልጣን ዓሊሚራህ ቤተ-መንግሥት።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X