ኢትዮጵያ ኤል ኒኖ ባስከተለው የውሃ እጥረት ሳቢያ ለቢትኮይን ማይኒንግ የሚቀርበውን የኤሌክትሪክ ኃይል በ75% ቀነሰች

© telegram sputnik_ethiopiaኢትዮጵያ ኤል ኒኖ ባስከተለው የውሃ እጥረት ሳቢያ ለቢትኮይን ማይኒንግ የሚቀርበውን የኤሌክትሪክ ኃይል በ75% ቀነሰች
ኢትዮጵያ ኤል ኒኖ ባስከተለው የውሃ እጥረት ሳቢያ ለቢትኮይን ማይኒንግ የሚቀርበውን የኤሌክትሪክ ኃይል በ75% ቀነሰች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 17.09.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ኤል ኒኖ ባስከተለው የውሃ እጥረት ሳቢያ ለቢትኮይን ማይኒንግ የሚቀርበውን የኤሌክትሪክ ኃይል በ75% ቀነሰች

እርምጃው የወቅቱ የኤል ኒኖ የአየር ሁኔታ ክስተት ወደ ሃይድሮ ኤሌክትሪክ ግድቦች የሚገባውን የውሃ መጠን በ20% መቀነሱን ተከትሎ የመጣ ነው።

​የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አሸብር ባልቻ ውሳኔው ለመኖሪያ ቤቶች እና ለፋብሪካዎች ኃይል ለመቆጠብ እንደተወሰደ ገልጸዋል።

​ተቋሙ ከ39 የቢትኮይን ማዕድን ማውጫዎች ጋር የገባውን የኃይል ስምምነት በጥቅምት ወር እንደሚገመግም እና ካለው የውሃ መጠን አንጻር ለቢትኮይን ማይኒንግ ኩባንያዎች እንዲሁም ለጎረቤት ሀገራት የሚያቀርበውን የኤሌክትሪክ ኃይል ሊቀንስ እንደሚችል ተጠቁሟል።

የቢትኮይን ማይኒንግ ኩባንያዎች ባለፈው የበጀት ዓመት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገቢ 35% የሚሆነውን እንደሚሸፍኑ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ሀገሪቱ ከምታመርተው 9 ሺህ 730 ሜጋ ዋት ጠቅላላ ኃይል ውስጥ አንድ ሦስተኛውንም ሲጠቀሙ ቆይተዋል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0