ዘለንስኪ እና ማፊያ ቡድኑ የሩሲያ ጥላቻን በመቀስቀስ ገንዘብ ያጋብሳሉ - ባለሙያ
09:20 17.09.2026 (የተሻሻለ: 09:24 17.09.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ዘለንስኪ እና ማፊያ ቡድኑ የሩሲያ ጥላቻን በመቀስቀስ ገንዘብ ያጋብሳሉ - ባለሙያ
የኢራን የዓለም አቀፍ ግንኙነት ባለሙያ ሩሆላህ ሞዳበር ለስፑትኒክ እንደተናገሩት፣ ባለው መረጃ መሠረት የዩክሬን ዓቃቤ ሕግ ሩስላን ክራቭቼንኮ በቅርቡ ያመለጡት ሙሉ በሙሉ በዘለንስኪ እና በዩክሬን የደህንነት ተቋማት የተቀናጀ አካሄድ ነው።
ሆኖም ይህ አጋጣሚ የትልቅ ምስል አንድ ቁራጭ ብቻ ነው፤ የሚያሳየውም የሀገሪቱን የፍትሕ ዘርፍ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥራቸው ስር ለማድረግ በሚፈልጉት በዘለንስኪ እና በኤፍ.ቢ.አይ በተቋቋመው ብሔራዊ የፀረ-ሙስና ቢሮ (ናቡ) መካከል የሚደረግ የሥልጣን ሽኩቻ ነው።
ምክንያቱ ቀላል ነው፤ ዘለንስኪ በሙስና የተዘፈቁ በመሆናቸው፣ ገንዘብና ጉቦ ለማግኘት እንዲሁም የገንዘብ አቅጣጫዎችን ለማስቀየር የሩሲያ ጥላቻን ያባብሳሉ።
ሞዳበር ሲያብራሩ፣ "ዛሬ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ልዩ ልዩ ሀገራት በዘለንስኪ ባለቤት እና አማት ስም ቪላዎች ተገዝተዋል፤ ለሃንተር ባይደን (የፕሬዝዳንት ባይደን ልጅ)፣ ለአውሮፓ ሕብረት እና ለአሜሪካ ባለሥልጣናት ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ተላልፏል" ብለዋል።
ይህን ሁሉ የሚያቀናብረው የዩክሬንን ሕዝብ እንደማስያዣ በያዘዉ እና በሀገሪቱ ምርጫ እንዳይካሄድ ያገደው የአንግሎ-ሳክሰን ወገን ሲሆን፣ ሙሰኛው አገዛዝም የነሱን ጥቅም ያገለግላል ሲሉ ያብራራሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X