የብሪክስ አዲስ ልማት ባንክ በአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ቢሮውን ቢከፍት ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካ ጥቅም አለው – ኢትዮጵያዊ ተንታኝ
08:03 17.09.2026 (የተሻሻለ: 08:04 17.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የብሪክስ አዲስ ልማት ባንክ በአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ቢሮውን ቢከፍት ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካ ጥቅም አለው – ኢትዮጵያዊ ተንታኝ
አዲስ አበባ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ መዲና በመሆኗ የባንኩ መከፈት የአኅጉሩን ሀገራት የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በእጅጉ እንደሚያመቻች የሕግ፣ የፖለቲካ እና የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኙ ዶ/ር ብሩክ መላኩ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ የብሪክስ አዲስ ልማት ባንክ አኅጉራዊ ቢሮ በአዲስ አበባ ለማስተናገድ ያቀረበችውን ጥያቄ አስመልከተው በሰጡት አስተያየት ያነሷቸው ተጨማሪ ነጥቦች፦
የዲፕሎማሲ እድልን መጠቀም፦ አዲስ አበባ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ መዲና በመሆኗ አኅጉራዊ የኢኮኖሚና የፋይናንስ ጉዳዮችን በቅርበትና በቀላሉ ለማስፈጸም ያስችላል።
የፋይናንስ ፍላጎትን መደገፍ፦ የባንኩ መኖር የአፍሪካን የመሠረተ ልማትና የፋይናንስ ፍላጎት መዋቅር በመቀየር ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል።
የኢኮኖሚ እንቅፋቶችን ማንሳት፦ በአኅጉሪቱ እና በብሪክስ ሀገራት መካከል ያሉ የተለያዩ የኢኮኖሚና የንግድ ማነቆዎችን ለመቅረፍ ይረዳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X