ኡጋንዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እንድትስፋፋ ድጋፍ እንደምታደርግ ተዘገበ
20:05 16.09.2026 (የተሻሻለ: 20:14 16.09.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኡጋንዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እንድትስፋፋ ድጋፍ እንደምታደርግ ተዘገበ
ይህ ድጋፍ የተገለጸው የቤተክርስቲያኗ የምሥራቅ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና በሃገሪቱ የኢትዮጵያ አምባሳደር ከኡጋንዳዋ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄሲካ አሉፖ ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት መሆኑን የቤተክርስቲያኗ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
የውይይቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
🟠 የቤተክርስቲያኗ ተወካዮች የኡጋንዳ መንግሥት ለስደተኞች፣ ለሃይማኖት ነፃነት እና ለቤተክርስቲያኗ እድገት ላደረገው እገዛ ምስጋና አቅርበዋል።
🟠 ቤተክርስቲያኗ በአሁኑ ወቅት አገልግሎቷን በሀገሪቱ እያስፋፋች በመሆኗ የመንግሥት አጋርነትና ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥያቄ አቅርባለች።
🟠 ምክትል ፕሬዝዳንት ጄሲካ አሉፖ የሃይማኖት ተቋማት ለሀገርና ለሕዝብ ሰላም ያላቸውን ሚና አጉልተው አሳይተዋል።
🟠 የጸሎት ሥነ ሥርዓቶች ሳይስተጓጎሉ እንዲከናወኑ እና የቤተክርስቲያኗ የማስፋፋት ሥራ እንዲሳካ መንግሥታቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X