የኢትዮጵያ ሕክምና አዲሱ ስኬት፦ የኢትዮጵያ ድንገተኛ ሕክምና ቡድን ከአፍሪካ ቀዳሚው የሚያደርገውን ታሪካዊ እውቅና ጨበጠ

ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ ሕክምና አዲሱ ስኬት፦  የኢትዮጵያ ድንገተኛ ሕክምና ቡድን ከአፍሪካ ቀዳሚው የሚያደርገውን ታሪካዊ እውቅና ጨበጠ

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የድንገተኛ ሕክምና "ዓይነት 1 የቋሚ ቦታ ድንገተኛ ሕክምና ቡድን" እውቅና ማግኘቱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡

 

እውቅናው የሚከተሉት ፋይዳዎች ይኖሩታል፦

 

ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ፦ በየትኛውም የዓለም ክፍል ድንገተኛ አደጋዎች (የተፈጥሮም ሆነ የሰው ሠራሽ) ሲከሰቱ ፈጣን የሕክምና እርዳታ የመስጠት ሙሉ ብቃትና ፈቃድ ያገኛል።

 

አስተማማኝ የሕይወት አድን አገልግሎት፦ በአስቸኳይ ጊዜያት ጥራት ያለውና ፈጣን ሕክምና በመስጠት የዜጎችን ሕይወት የመታደግ አቅምን በከፍተኛ ደረጃ ያሳድጋል።

 

ቀጣይነት ያለው የጤና ሥርዓት፦ አደጋዎችን የሚቋቋም፣ ጠንካራና የዘመነ የሀገር ውስጥ የጤና ሥርዓት ለመገንባት መንገድ ይጠርጋል።

ዓለም አቀፍ ደረጃና እምነት፦ የኢትዮጵያ የሕክምና ባለሙያዎችና ተቋማት በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸውን ተወዳዳሪነት፣ ዝግጁነት እና ተጋላጭነት ከፍ ያደርጋል።

 

አኅጉራዊ አለኝታ፦ ከአፍሪካ የመጀመሪያው የሲቪል ድንገተኛ ሕክምና ቡድን በመሆኑ፣ ለአኅጉሪቱ ፈጣን ድጋፍ በመስጠት ረገድ ቀዳሚ ሚና ይጫወታል።

 

ይህ ስኬት የዓመታት ትጋትና ትዕግሥት፣ እንዲሁም በጤና ባለሙያዎች፣ በተቋሞች እና በአጋሮች የተደረገ ትልቅ ሥራ ውጤት መሆኑን የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ገልጸዋል፡፡

 

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0