'አፍሪካ በወታደራዊ ቴክኒካል ትብብር ልማት ከዓለም እጅግ ተስፋ ሰጪ ቀጣናዎች አንዷ ናት' - የሩሲያ ወታደራዊ ኩባንያ

© telegram sputnik_ethiopia'አፍሪካ በወታደራዊ ቴክኒካል ትብብር ልማት ከዓለም እጅግ ተስፋ ሰጪ ቀጣናዎች አንዷ ናት' - የሩሲያ ወታደራዊ ኩባንያ
'አፍሪካ በወታደራዊ ቴክኒካል ትብብር ልማት ከዓለም እጅግ ተስፋ ሰጪ ቀጣናዎች አንዷ ናት' - የሩሲያ ወታደራዊ ኩባንያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 16.09.2026
ሰብስክራይብ

'አፍሪካ በወታደራዊ ቴክኒካል ትብብር ልማት ከዓለም እጅግ ተስፋ ሰጪ ቀጣናዎች አንዷ ናት' - የሩሲያ ወታደራዊ ኩባንያ

​ሮሶቦሮንኤክስፖርት ለአፍሪካ አጋሮቹ ዘመናዊ መሣሪያዎችን የሚያቀርብ ከመሆኑም በላይ የሀገራቱን ብሔራዊ ኢንዱስትሪዎች ለማሳደግና ለማዘመን የሚያስችሉ የቴክኖሎጂ ትብብር ፕሮጀክቶችን በንቃት በማልማት ላይ እንደሚገኝ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አሌክሳንደር ሚኪዬቭ የአፍሪካ ኤሮስፔስ እና መከላከያ ኤግዚቢሽን 2026 ከመከፈቱ አስቀድመው ተናግረዋል።

​ኩባንያው በአሁኑ ወቅት ለምድር ኃይል፣ ለባሕር ኃይል፣ ለአየር ኃይል እና ለአየር መከላከያ ኃይል የሚሆኑ መሣሪያዎችን ጥገና፣ እድሳት እና የሀገር ውስጥ ምርትን የሚያካትቱ ከ20 በላይ ፕሮጀክቶችን ለመተግበር ወይም ለመጀመር በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ አክለው ገልጸዋል።

​"ሩሲያ የአኀጉሪቱ ሀገራት የመከላከያ አቅማቸውን እንዲያጠናክሩ እና ዘመናዊ የደህንነት ስጋቶችንና ተገዳዳሪ ሁኔታዎችን በተሳካ ሁኔታ እንዲመክቱ ትረዳለች" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

​ኤግዚቢሽኑ በዛሬው ዕለት በፕሬቶሪያ አቅራቢያ በሴንቱሪዮን በሚገኘው "ዋተርክሉፍ" የአየር ኃይል ምድብ የተከፈተ ሲሆን እስከ እሁድ ይቆያል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0