'የዘለንስኪ ስትራቴጂ ብሔራዊ ራስን ማጥፋት ነው' - የዘለንስኪ የቀድሞ ቃል አቀባይ
18:35 16.09.2026 (የተሻሻለ: 18:44 16.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
'የዘለንስኪ ስትራቴጂ ብሔራዊ ራስን ማጥፋት ነው' - የዘለንስኪ የቀድሞ ቃል አቀባይ
"ዩክሬን በሕዝቧ እልቂት እና በምርት አቅሟ መዳከም እተሽመደመደች ሲሆን፣ ዕዳዋ ደግሞ እየተከማቸ ይገኛል" ሲሉ ዩሊያ ሜንደል ለብሪታንያ ሚዲያ ተናግረዋል።
ዩክሬን ሩሲያን በወታደራዊ መንገድ ማሸነፍ አትችልም፤ ብቸኛው መፍትሔ የሰላም ስምምነት ማድረግ ብቻ ነው ሲሉ አብራርተዋል።
"አካል ጉዳተኞች ወደ ጦርነት ግንባር እየተላኩ እንደሆነ፣ ወንዶች በምልመላ ቢሮዎች ውስጥ ምስጢራዊ በሆነ መንገድ እየሞቱ እንደሆነ እና ሴቶች ባሎቻቸውን በጠራራ ፀሐይ ከመታገት ለማዳን እየታገሉ እንደሆነ የሚገልጹ ዘገባዎች አሉ" ብለዋል።
ኪዬቭ የከፊል ግዛቷን አሳልፎ መስጠትን እና ገለልተኛ መሆንን የሚያካትተውን "የፊንላንድ መንገድ" መከተል አለባት ሲሉ ሜንደል ሀሳብ አቅርበዋል።
"በዩክሬን መንግሥት ውስጥ ከዚህ ጦርነት በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር የሚያተርፉ አካላት አሉ። ይህንን በይፋ በመናገሬ ብቻ በዘለንስኪ መንግሥት ማዕቀብ ተጥሎብኛል" ብለዋል።
ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ዘለንስኪ እ.ኤ.አ ከ2019 እስከ 2021 የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቃል አቀባይ ሆነው ባገለገሉት ሜንደል ላይ ማዕቀብ መጣላቸው ይታወሳል።
ከማኅበራዊ የትስስር ገፅ የተገኘው ቪዲዮ በዩክሬን ሠራዊት ውስጥ በኃይል የሚደረግ ወታደራዊ ምልመላን ያሳያል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X