ኢትዮጵያ ለኬንያ የምታቀርበውን የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን ወደ 400 ሜጋዋት ልታሳድግ ነው

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ለኬንያ የምታቀርበውን የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን ወደ 400 ሜጋዋት ልታሳድግ ነው

 

ኢትዮጵያ ለኬንያ የምታቀርበውን የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን በመጪው ታህሳስ ወር ከ200 ወደ 400 ሜጋዋት ልታሳድግ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።

 

ዋና ዋና መግለጫዎች፡-

 

የቴክኒክ ዝግጅት፡- ተጨማሪ ኃይል ከመላኩ በፊት የሙከራ ሥራውን የሚያከታተል የጋራ የቴክኒክ ቡድን ወደ ሥራ ገብቷል።

 

የግሪድ ጥንቃቄ፡- የኬንያ ኤሌክትሪክ ግሪድ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የተያያዘ በመሆኑ የግሪድ አለመረጋጋት እንዳይከሰት የጋራ ጥንቃቄ እየተደረገ ይገኛል።

 

የታንዛኒያ የኃይል ሽያጭ፡- በሙከራ ደረጃ 100 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ለታንዛኒያ እየቀረበ ሲሆን፤ በኬንያና ታንዛኒያ መካከል ያለው የመሠረተ ልማት ማሻሻያ ሲጠናቀቅ መደበኛ የኃይል ሽያጭ ይጀመራል።

 

በምሥራቅ አፍሪካ ያለውን የኃይል ትስስር ለማጠናከርና የውጭ ንግድ አቅምን ለማሳደግ ከቀጣናው ሀገራት ጋር በአዲስ አበባ የተካሄደው ምክክር ተጠናቋል።

ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተገኘው ቪዲዮ የኢትዮ-ኬንያ የኃይል ኮንቨርተር ጣቢያን ያሳያል፡፡

 

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0