ኢትዮጵያ ለተመድ የንግድ እና ልማት ጉባኤ የንግድና ልማት ቦርድ መዋቅራዊ ሽግግር ጠንካራ ዓለም አቀፍ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቀረበች

© telegram sputnik_ethiopiaኢትዮጵያ ለተመድ የንግድ እና ልማት ጉባኤ የንግድና ልማት ቦርድ መዋቅራዊ ሽግግር ጠንካራ ዓለም አቀፍ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቀረበች
ኢትዮጵያ ለተመድ የንግድ እና ልማት ጉባኤ የንግድና ልማት ቦርድ መዋቅራዊ ሽግግር ጠንካራ ዓለም አቀፍ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቀረበች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 16.09.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ለተመድ የንግድ እና ልማት ጉባኤ የንግድና ልማት ቦርድ መዋቅራዊ ሽግግር ጠንካራ ዓለም አቀፍ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቀረበች

​ኢትዮጵያ በጄኔቫ በተካሄደው 73ኛው የቦርዱ አጠቃላይ ክርክር ላይ፣ ታዳጊ ሀገራት የኢኮኖሚ ማሻሻያዎቻቸውን ወደ ምርታማ ኢንቨስትመንት፣ መዋቅራዊ ሽግግር እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ለመቀየር ጠንካራ ዓለም አቀፍ ትብብርና የልማት ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቀረበች።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት አምባሳደር ንጉሥ ከበደ፣ ሀገራቸው ለብዙ ወገን ትብብር ያላትን ቁርጠኝነት ገልጸው፣ በሕግ ላይ የተመሠረተ እና ልማትን ማዕከል ያደረገ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ሥርዓት አስፈላጊነትን አብራርተዋል።

​ልዑካን ቡድኑ አምራቾችን ከቀጠናዊና ዓለም አቀፍ ገበያዎች ጋር ለማያያዝ የትስስር እና የንግድ ማመቻቸት አስፈላጊነትን ያጎላ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጠና ያላትን ቁርጠኝነት ማረጋገጧን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0