ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና ሥር ንግድን የሚያሳልጡ ጊዜና ወጪን ቆጣቢ ሥርዓቶችን ልታጸድቅ ነው
12:05 16.09.2026 (የተሻሻለ: 12:14 16.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና ሥር ንግድን የሚያሳልጡ ጊዜና ወጪን ቆጣቢ ሥርዓቶችን ልታጸድቅ ነው
በአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ማዕቀፍ ስር የሚደረገውን የዕቃ ንግድ ለማቀላጠፍ የተዘጋጁ የደረጃ በደረጃ መመሪያ እና ዲጂታል የንግድ መረጃ ፖርታል ለማፅደቅ የሚያስችል ምክክር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
ፖርታሉ እና መመሪያው ምን ፋይዳ አላቸው?
▪ ሁሉንም መረጃ በአንድ ቦታ፦ የሕግ፣ የደንብ፣ የጉምሩክ ሂደቶችና የሰነድ ዝግጅት መረጃዎችን በቀላሉ ማግኘት ያስችላሉ።
▪ ጊዜና ወጪን ቁጠባ፦ ውስብስብ አሠራሮችን በማስቀረት ንግድን ፈጣንና አነስተኛ ወጪ የሚጠይቅ ያደርጋሉ።
▪ ለአነስተኛ ንግዶች ትልቅ ዕድል፦ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች፣ ሴቶች እና ወጣቶች የሚያጋጥማቸውን የመረጃ ክፍተት ይሞላሉ።
▪ ያልተገደበ ገበያ፦ የኢትዮጵያን ነጋዴዎች የአፍሪካን ሰፊ ገበያ ሙሉ በሙሉ እና በቀላሉ እንዲጠቀሙ መንገድ ይከፍታሉ፡፡
ኢትዮጵያ እስከ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 2026 ድረስ በአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ማዕቀፍ ስር የ23.6 ሚሊዮን ዶላር የወጪ ንግድ ማከናወኗን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X