በአሜሪካ የኢራን ጦርነት ምክንያት የተቀሰቀሰው ዓለም አቀፍ የነዳጅ ውጥረት እያየለ መምጣቱ ተዘገበ
08:50 16.09.2026 (የተሻሻለ: 08:54 16.09.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በአሜሪካ የኢራን ጦርነት ምክንያት የተቀሰቀሰው ዓለም አቀፍ የነዳጅ ውጥረት እያየለ መምጣቱ ተዘገበ
የሆርሙዝ ወሽመጥ አለመከፈቱን ተከተሎ፣ በነዳጅ ገበያ ላይ ያለው ሁኔታ ከቁጥጥር ውጪ እየሆነ በመምጣቱ ከፍተኛ የአሜሪካ የነዳጅ ኩባንያ ሥራ አስፈጻሚዎች ሥጋታቸውን ገልጸዋል።
ወደ ቀይ ባሕር ዳርቻ የሚዘረጋው የሳዑዲ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ያሉ አማራጭ መንገዶች መስተጓጎል እና በዓለም ዙሪያ ያለው የንግድ የነዳጅ ክምችት መሟጠጥ፣ አሁን ላይ "የዋጋ እና የአቅርቦት ሥጋትን ለመቀነስ" የሚያስችል ምንም ዓይነት መንገድ የለም ማለት እንደሆነ ዎል ስትሪት ጆርናል የሼቭሮን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ማይክ ዊርዝን ጠቅሶ ዘግቧል።
ቀደም ሲል የነበሩት ማቃለያ ክምችቶች በመጠናቀቃቸው፣ የነዳጅ ዋጋ ምን ያህል ሊያሽቅብ እንደሚችል ባይታወቅም፣ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ይቀንሳል ተብሎ ግን አይጠበቅም ሲሉ ዊርዝ አስጠንቅቀዋል።
"ነገሮች የሚረግቡበትን ምክንያት ማየት ብችል ደስ ይለኝ ነበር፤ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ያ ሲሆን ማየት አዳጋች ነው" ሲሉ መስከረም 1 በቴክሳስ በተካሄደው የኃይል ጉባኤ ላይ ተናግረዋል።
እንደ ዎል ስትሪት ጆርናል ዘገባ፣ አሜሪካ የራሷን የነዳጅ ማጣራት አቅም በመጨመር እና በቬኔዙዌላ ያለውን የነዳጅ ምርት በማሳደግ ሁኔታውን ለማስተካከል ልትሞክር ትችላለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X