ከማዕከል እስከ ሩቅ ገጠር፦ የድንገተኛ ሕክምና አቅርቦት ስርጭትን የሚያፋጥን አዲስ ብሔራዊ ዕቅድ
17:35 15.09.2026 (የተሻሻለ: 17:44 15.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ከማዕከል እስከ ሩቅ ገጠር፦ የድንገተኛ ሕክምና አቅርቦት ስርጭትን የሚያፋጥን አዲስ ብሔራዊ ዕቅድ
የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በአደጋ ጊዜ የሚፈለጉ የሕክምና ግብዓቶች በፍጥነትና በጥራት ሕብረተሰቡ ዘንድ እንዲደርሱ የሚያስችል "የብሔራዊ የሕክምና መከላከያ እርምጃዎች ዕቅድ" እያዘጋጀ እንደሚገኝ አስታወቀ።
ዕቅዱ ለሕብረተሰቡ የሚያስገኘው ዋና ዋና ጥቅሞች፦
🟠 ድንገተኛ የጤና አደጋዎች በሚከሰቱበት ጊዜ አስፈላጊ የሆኑ መድኃኒቶችና የሕክምና መገልገያዎች በፍጥነት፣ በተገቢው መጠን እና በሚያስፈልገው ቦታ እንዲደርሱ ያደርጋል።
🟠 ከማዕከል እስከ ሩቅ ገጠርና የጤና ተቋማት ድረስ ፍትሐዊና ቀልጣፋ የስርጭት ሥርዓት ይዘረጋል።
🟠 አደጋ ከመከሰቱ በፊት የግብዓት ፍላጎቶችን በቅድሚያ በመለየትና በመያዝ የሕብረተሰቡን ደህንነት አስተማማኝ ያደርጋል።
🟠 የሕክምና ቁሳቁሶች ብክነትን በመቀነስ ሁልጊዜም ለድንገተኛ አደጋ ዝግጁ የሆነ አቅም ይፈጥራል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X