“በ21 ከተሞች ላይ የወጣቶች ሊግ እንመሰርታለን” - የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት

ሰብስክራይብ

“በ21 ከተሞች ላይ የወጣቶች ሊግ እንመሰርታለን” - የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት

በ21 የተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ከ17 ዓመት በታች የወጣቶች ሊግ ለመመሥረት መታቀዱን ኢሳያስ ጂራ በመካሄድ ላይ ባለው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 18ኛ መደበኛ እና የምርጫ ጠቅላላ ጉባኤ መክፈቻ ሥነ-ስርዓት ላይ ይፋ አድርገዋል።

በንግግራቸውም ወጣት ተተኪዎችን በማፍራት ረገድ ከ5 ዓመታት በፊት የተጀመረው የ“አንድ ኳስ ለአንድ ሠልጣኝ” ፕሮጀክት ፍሬ ማፍራቱን ገልጸዋል። ስራው ከ4 ዓመታት በኋላ ወደ ሊግ ለማደግ እና ኢትዮጵያ ከ22 ዓመታት ቆይታ በኋላ ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ እንድትመለስ ማስቻሉንም አብራርተዋል።

ሊጉ ሁሉንም ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ያመለከቱት ፕሬዝዳንቱ፣ ለውድድሩ እስከ 105 ሚሊዮን ብር ዓመታዊ በጀት እንደሚያስፈልግም መናገራቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል።

በስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ የተቀረተሰ ቪዲዮ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0