የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዲስ ፕሬዝዳንት ሊመርጥ ነው

ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዲስ ፕሬዝዳንት ሊመርጥ ነው

 

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 18ኛ መደበኛ እና የምርጫ ጠቅላላ ጉባኤውን ማካሄድ መጀመሩን የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል።

 

የስብሰባው ዋና ዋና ነጥቦች፦

ፌዴሬሽኑን ለቀጣዮቹ 4 ዓመታት በፕሬዝዳንትነት የሚመራውን ግለሰብ ይመረጣል፡፡

ላለፉት 8 ዓመታት ፌዴሬሽኑን በፕሬዝዳንትነት የመሩት ኢሳያስ ጂራ ለቦታው ብቸኛ እጩ ሆነው ቀርበዋል።

 

በጉባኤው የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጂራ፣ የዋሊያዎቹ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ፣ የክልልና የከተማ ፌዴሬሽን እንዲሁም የክለብ አመራሮች፣ የኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና የሊግ አክሲዮን ማኅበር ኃላፊዎች፣ የቀድሞ ተጫዋቾች፣ አሰልጣኞች እና የስፖርት ሳይንስ ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡

በስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ የተቀረጸ ቪዲዮ

 

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0