እያደገ ከሚሄደው የሻንጋይ ትብብር ድርጅት ባለብዙ-ዋልታ ሥርዓት አፍሪካ ምን ትማራለች? - ታንዛኒያዊ ባለሙያ መልስ አላቸው
08:03 15.09.2026 (የተሻሻለ: 08:04 15.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
እያደገ ከሚሄደው የሻንጋይ ትብብር ድርጅት ባለብዙ-ዋልታ ሥርዓት አፍሪካ ምን ትማራለች? - ታንዛኒያዊ ባለሙያ መልስ አላቸው
ዓለም ወደ አዲስ የዓለም አቀፍ ሥርዓት እየተሸጋገረች ባለችበት በአሁኑ ወቅት፣ አፍሪካ ከጥሬ ዕቃ ምንጭነት አልፋ ጠንካራ አጋር መሆን አለባት ሲሉ የፖለቲካ ተንታኙ ጎድፍሬይ ምቹንጉለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ቻይና የንግድ እና የመሠረተ ልማት ትስስሮችን ስትመራ፣ ሩሲያ ደግሞ በኃይል እና በኒውክሌር ቴክኖሎጂ ግንባር ቀደም እንደሆነች የጠቆሙት ተንታኙ፣ አፍሪካ ከኮባልት እስከ ዩራኒየም ያሉ ወሳኝ ሀብቶች ባለቤት መሆኗን በሻንጋይ ትብብር ድርጅትን ስኬቶች እና በማደግ ላይ ባለው የባለብዙ ዋልታ ዓለም ውስጥ የታዳጊ ሀገራትን ሊከተሏቸው የሚችሉ ስልቶችን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።
"አፍሪካ የንግድ፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የመሠረተ ልማት፣ የኢነርጂ እና የግል ዘርፉን በማገናኘት የእሴት ሰንሰለቶችን ለመገንባት ከሻንጋይ ትብብር ድርጅት ተሞክሮ መማር ትችላለች" ሲሉ ተንታኙ ጠቁመዋል።
እንደ ምቹንጉ ገለጻ፣ የአፍሪካ ሀገራት ተወዳዳሪ እና ራሱን የቻለ ኢኮኖሚ ለመገንባት እንዲሁም በባለብዙ- ዋልታ ዓለም ውስጥ ድርሻቸውን ለማረጋገጥ እነዚህን ዓለም አቀፍ ለውጦች በአግባቡ መጠቀም አለባቸው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X