ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሁለት ዓመት የኃይል ማመንጨት ከአቅድ በላይ በ17% ጨመረ - ዓለም አቀፍ ጥምረት

ሰብስክራይብ

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሁለት ዓመት የኃይል ማመንጨት ከአቅድ በላይ በ17% ጨመረ - ዓለም አቀፍ ጥምረት

 

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዓመት ሙሉ የኃይል ማመንጨቱን አስመልክቶ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዓለም አቀፍ የትብብር ጥምረት ባወጣው መግለጫ ለሀገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቋል፡፡

 

የጥምረቱ መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች፦

 

🟠 ኢትዮጵያ በ2018 የበጀት ዓመት 35 ሺህ 671 ጊጋዋት ሠዓት ኤሌክትሪክ አምርታለች፡፡

 

🟠 ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የ51.5 በመቶ የምርት ድርሻ በመያዝ ከአቅድ በላይ የ17% ብልጫ አሳይቷል።

 

🟠 ለኬንያ፣ ጅቡቲ እና ሱዳን ወደ 2,500 ጊጋዋት ሠዓት ኤሌክትሪክ በመላክ የቀጣናዊ ኃይል ትስስሩን አጠናክሯል።

 

🟠 ከኃይል ሽያጭ የሚገኘው ገቢ ለሀገር ውስጥ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታና መሠረተ ልማት እንዲውል ጠይቀዋል፡፡

 

🟠 ኃይል ከክሪፕቶ ሚኒንግ ይልቅ ለብዙ የሥራ ዕድል ፈጣሪ ኢንዱስትሪዎች ቅድሚያ እንዲሰጥ ጥምረቱ ጥሪ አቅርቧል።

 

የሕዳሴ ግድብ ዓለም አቀፍ የትብብር ጥምረት በኢትዮጵያና በውጭ ሀገራት (አሜሪካ፣ ካናዳ፣ እንግሊዝ፣ ኖርዌይ) በሚኖሩ ባለሙያዎች የተመሠረተ፣ ግድቡንና ፍትሐዊ የናይል ውኃ አጠቃቀምን የሚደግፍ ነፃ ስብስብ መሆኑን የሀግር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0