ሩሲያ በመጪው ጥቅምት በዩክሬን ጉዳይ ላይ ከሚደረጉ የሦስትዮሽ ንግግሮች ራሷን አታገልም - የክሬምሊን ቃል አቀባይ
16:26 13.09.2026 (የተሻሻለ: 16:34 13.09.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያ በመጪው ጥቅምት በዩክሬን ጉዳይ ላይ ከሚደረጉ የሦስትዮሽ ንግግሮች ራሷን አታገልም - የክሬምሊን ቃል አቀባይ
ሩሲያ በየመን ያሉ ሁኔታዎችን የምትከታተል መሆኑን የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ገልጸው፣ እዚያ ያለው ሁኔታ በገልፍ ቀጣና ከተከሰተው አለመረጋጋት የመጣ ነው ብለዋል።
ቃል አቀባዩ በተጨማሪም የሚከተሉትን ነጥቦች አንስተዋል፦
◾ ብሪክስ ከፍተኛ ጉልበት እያገኘ ነው፤ እንዲሁም ከባድ እና መሠረታዊ ጉዳዮችን እያነሳ ይገኛል፡፡
◾ በክፍያ እና በፋይናንስ ዙሪያ ለሩሲያ አስፈላጊ የሆኑ ዋና ዋና ድንጋጌዎች በብሪክስ ጉባኤ መግለጫ ውስጥ ተካተዋል፡፡
◾ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ኢራን እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ለብሪክስ ጉባኤ መግለጫ የሚሆን የጋራ ቋንቋ እንዲስማሙ መርዳታቸውን ሩሲያ በበጎነት ትቀበለዋለች፡፡
◾ ሩሲያ ለጊዜው ከሳዑዲ አረቢያ ጋር በከፍተኛ አመራር ደረጃ የሚደረግ ግንኙነት እቅድ የላትም፡፡
◾ የፕሬዝዳንት ፑቲን የሚቀጥለው ጉዞ ወደ አንዱ የሩሲያ ክልል ይሆናል፡፡
◾ ፑቲን በእርግጥ የእረፍት ቀን የላቸውም፤ ይህ ሁኔታ ሰለማይቀየር "ልመዱት፡፡"
◾ የፕሬዝዳንቱ የማያቋርጥ የሳምንቱ መጨረሻ የሥራ ቀናት የአጋጣሚዎች መገጣጠም ብቻ ናቸው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
