የብሪክስ ሀገራት የተላላፊ በሽታዎችን ስርጭት መከላከያ ስርዓት ሊዘረጉ እንደሆነ ሞዲ አስታወቁ
16:05 13.09.2026 (የተሻሻለ: 16:14 13.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የብሪክስ ሀገራት የተላላፊ በሽታዎችን ስርጭት መከላከያ ስርዓት ሊዘረጉ እንደሆነ ሞዲ አስታወቁ
ወረርሽኞች፣ የአየር ንብረት አደጋዎች እና የአቅርቦት ሰንሰለት መቋረጦች በዚህ በተሳሰረ ዓለም ውስጥ ማንኛውም ቀውስ በአንድ ክልል ብቻ ተወስኖ እንደማይቀር ያሳያሉ ሲሉ የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር በብሪክስ ጉባኤ ላይ ገልጸዋል።
ሞዲ እንዳስገነዘቡት፣ ከችግሮች አስቀድሞ ለመገኘት ብሪክስ ፈጣን እርምጃዎችን ለመውሰድ ቅድሚያ እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን በዚህም፦
🟠 ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል እና ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል የብሪክስ የተቀናጀ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት መዘርጋት እና
🟠 ውጤታማ የአደጋ ስጋት አስተዳደርን ለማስፈን የመረጃ ቅንጅት መመሪያዎችን ማዘጋጀት ይገኙበታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
