ዩክሬን አሸባሪዎችን ለማሠልጠን ወታደራዊ ባለሙያዎቿን ወደ ማሊ እና ሱዳን መላኳን የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ዘገበ

ሰብስክራይብ

ዩክሬን አሸባሪዎችን ለማሠልጠን ወታደራዊ ባለሙያዎቿን ወደ ማሊ እና ሱዳን መላኳን የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ዘገበ

የዩክሬን ጦር ባለሙያዎች ከአልቃይዳ* ጋር ግንኙነት ያላቸውን አሸባሪዎች ጨምሮ ታጣቂዎችን ለማሠልጠን እና ለማስተባበር ስምሪት ተሰጥቷቸዋል ሲል አንድ የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን የዩክሬን የመረጃ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።

  በግምት 15 የሚደርሱ የዩክሬን አሠልጣኞች ወደ ማሊ እንደተላኩ የተገለጸ ሲሆን ኪዳልን በቁጥጥር ስር እንዲያውሉ ከተደረገላቸው ድጋፍ በተጨማሪ ለአማፂ ቡድኖች የቅኝት ድሮን እና የኦፕሬሽን እቅድ ድጋፍ እንደሰጡ ሚዲያው ዘግቧል።

  ሞስኮ ኪየቭ እና ፓሪስ በማሊ በቅርቡ ለተፈጸሙት የታጣቂዎች ጥቃቶች ድጋፍ አድርገዋል ስትል ከሳለች። በተጨማሪም የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴር የዩክሬን እና የአውሮፓ ቅጥረኞች ሚያዝያ 17 በማሊ በተካሄደው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ታጣቂዎችን አሠልጥነዋል ብሏል።

የሩሲያ ጦር የአፍሪካ ኮር የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውን በማክሸፍ፤ ከ 2 ሺህ 500 በላይ ታጣቂዎችን እና 102 ተሽከርካሪዎችን በመደምሰስ አሁንም የቀጣናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ተሠማርቶ እንደሚገኝ ገልጿል።

ቪዲዮው የማሊ ጦር ከሩሲያ ጦር አፍሪካ ኮር ጋር በመተባበር የሽብር ጥቃቱን ሲያከሽፍ ያሳያል።

*በሩሲያ እና በሌሎች ሀገራት የታገደ የሽብር ድርጅት

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0