ዓለም አቀፉ የወጣቶች ፌስቲቫል በሩሲያዋ የካተሪንበርግ ተጀመረ

ሰብስክራይብ

ዓለም አቀፉ የወጣቶች ፌስቲቫል በሩሲያዋ የካተሪንበርግ ተጀመረ

​ፌስቲቫሉ በሙያ ልምዳቸው መሠረት ለተመረጡ እንዲሁም በሚኖሩበት ዓለም መጪ ዘመን ተጽዕኖ ለማሳደር በጋራ ዓላማ ለተሰባሰቡ እና በማኅበራዊ ጉዳዮች ንቁ ተሳትፎ ላላቸው ወጣቶች መድረክ ሆኖ ያገለግላል።

​  ከ6,500 በላይ ተሳታፊዎች ከወዲሁ የደረሱ ሲሆን ተጨማሪ የልዑካን ቡድኖች መግባታቸውን ቀጥለዋል።

​ፌስቲቫሉ ለእውነተኛ ውይይት ምቹ ሁኔታ በመፍጠር በጋራ የተሻለ ዓለም ለመገንባት በቆረጡ ወጣቶች መካከል ዘላቂ ትስስር የመፍጠር ዓላማ አንግቧል። ተሳታፊዎቹ ዓለምን ለመለወጥ በሚያደርጉት ጥረት አጋሮች፣ ሀሳቦች እና ድጋፍ ፍለጋ የተሰባሰቡ ናቸው።

​የ2024ቱ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ፌስቲቫል 20,000 ተሳታፊዎችን ያሰባሰበ ሲሆን በግዜው ተዘጋጅተው ከነበሩ ሁሉ ከፍተኛ ቁጥር ውክልና ከነበራቸው የወጣቶች ዝግጅቶች መካከል አንዱ ሆኖ አልፏል። የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ፌስቲቫል ከ191 ሀገራት የተውጣጡ 10,000 ተሳታፊዎችን በማሳተፍ ከመስከረም 2 እስከ 7 በየካተሪንበርግ እየተካሄደ ይገኛል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0